ይህ ነው እስልምና  በዓለም ላይ በፍጥነት እየተስፋፉ በሚገኙ ሃይማኖ ቶች ዙሪያ ጥልቅ እይታ

ይህ ነው እስልምና በዓለም ላይ በፍጥነት እየተስፋፉ በሚገኙ ሃይማኖ ቶች ዙሪያ ጥልቅ እይታ

globe icon All Languages

Description

ይህ ነው እስልምና በዓለም ላይ በፍጥነት እየተስፋፉ በሚገኙ ሃይማኖ ቶች ዙሪያ ጥልቅ እይታ - በዙሪያህ ባሉ መገናኛ ብዙሃን በብዛት ክርክር በሚያስነሱ ሃይማኖቶች ዙሪያ ግልጽ የሆነ እይታ ማግኘት አያሳስብህምን?… እንደው ላፍታ ቆም ብለህ በዓለም የስታትስቲክስ መረጃ መሰረት ከሃይማኖቶች መካከል በስፋት እየተሰራጩና በፍጥነት ተቀባይነትን እያገኙ ካሉ ሃይማኖቶች መካከል ስለአንዱ በጥልቀት ማወቅ እንዳለብህ ግድ አይልህምን?… ስለሌሎች ማህበረሰቦች ባህል እንዲሁም ማህበረሰቦቹ ስለሕይወት፣ ሰለሃይማኖትና ሌሎች በዙሪያችን ስለሚገኙ ነገሮች ያላቸውን ፍልስፍና በማወቅህ ታላቅ ደስታና እርካታ አታገኝምን? ስለእስልምና ሃይማኖት ከተረጋገጡ ምንጮቹ መረጃዎችን ለማወቅና ካወቅክ በኋላ አእምሮህንና ችሎታህን ተጠቅመህ በእነሱ ላይ ለመወሰን ለነፍስህ እድል ትሰጣለህን? እንዲህ የምትመለከት ወይም ከእሱ ውስጥ አስፈላጊ የሆነ አንድ ነገር ወይም ደስ የሚያሰኝ ነገር የምትመለከት ከሆነ ይህ መጽሐፍ ለማግኘት የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ያግዛሃል፡፡